የአደይ እንጀራ
እስኪ ስለቻው ሆቴል ትዝታ ያላቹህ ጻፉ ቻው ሆቴል በነበርንበት ግዜ ስለአንጀራ ጋጋሪዋቻችን እነአደይ ጥበቃ እነተገኝን አለማስታወስ አይቻልም ።በተለይ በ1982 ዓ.ም ከፍተኛ የምግብ አጥረት ነበረብን እንጀራ ለማግኘት ብዙ ግዜ የመጨረሻ ፔሬድ እንፎርፋና ወይም ችግሩ የሚገባቸው መምህራን 15 ደቃቅ ቀድመው ሲለቁን ብቻ ነበር እነጀራ የምናገኘው አንደዚያም ሆኖ አብዛኛውን ጊዜ እንጀራ አልቆ ዳቦ በሽሮ ነበር የምንመገበው ከዚያ በኋላ ወደ ማደሪያችን ቻው ሆቴል ስንገባ እንጀራ የሚጋገርበት ቦታ ስለነበረ ጥበቃዋች እንጀራ ከጋጋሪዋች ይደብቁ ነበር አንድ ጓደኛችን እሱባለው ይባላል የማሽተት ችሎታው በእውነት በጣም ይገርመኛል የተደበቀውን እንጀራ የትም ቦታ ቢሆን ፈልጎ ያገኘዋል ብዙ ከተደበቀ 3እንጀራ ትንሽ ከሆነም አንድና ሁለት ከጥበቃዋቻችን እየተካፈልንና አየወሰድን በበርበሬ እየበላን ብዙ ጊዜ አሳለፍን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የሚደበቅበት ቦታ ጠፍቶን ይሁን ወይም እነሱም እንደኛ አልሳካ ብሏቸው እንጀራ ልናገኝ አልቻልንም
አንድ ቀን እራት በደንብ ስለማናገኝ ማታ በጣም ራበኝ ማጥናትም አልቻልኩም ለመተኛት ሞከርኩ እንቅልፍ አልወስድ አለኝ ከዚያ በኋላ አብረውኝ ከነበሩት ውስጥ በጋሻው ሂድና አደይ ማይ በልና እንጀራ ይሰጡሃል አልኩት በተባለው መሰረት ውሃ የምንጠጣበት የማርማራታ ጣሳ ነበረን እሱን ይዞ ሲጠይቅ ውሃውን ብቻ ቀድተው ሰጡት በፊት ግን ውሃ ስንጠይቅ እውነት የተፈጨ ጨው በእንጀራዉ አይን ተነስንሶ እንጀራው በስራት ታጥፍ ብዙ ጊዜ ይሰጡን ነበር በእውነት በጣም የተባረኩ እናቶች ነበሩን ሆኖም ያንቀን ተቆጣጣሪዎች ኖረውባቸው ይሁን ወይም በሌላ ምክንያት ምግብ ማግኘት በቀላሉ አልተቻለም ከዚያ በኋላ ከቤተሰብ ያመጣሁት በርበሬ ነበረኝ እሱባለው ና ይሄን በርበሬ ለእናደይ ስጥና እንጀራ ይዘህ ና ብየ እንደገና እሱባለውን ላኩት እሱም እንደለመድነዉ ጣሳውን ይዞና በርበሬውን ሰጥቶ አደይ ማይ አላቸው አንደኛዋ ጋጋሪ እንጀራውን አጥፋ እየተያዩ ሳይሰጡት ውሃውን ብቻ ሰጥታ ይቀራል ያኔ መተኛት ስላልቻልኩ ከተኛሁበት በመነሳት ጣሳዬን በመያዝ እንጀራ እንጀራውን እያየሁ አደይ ማይ አልኳቸው እነሱም ሁኔታው ስለገባቸው በጨው የተነሰነሰ እንጀራ በጣም ይጣፍጣል ተሰጥቶኝ በልተን የተኛሁት ጊዜም አይረሳኝም ።