Caution: Blogger names and names referred in the blogs may have been altered for privacy.
ገንዘብ ተልኮልዎታል
የዚህ አሉምኒ ታሪክ መቼም ተነግሮ አያልቅምና ከመካከላችን አንዱ የሆነው ወንድማችን ቀደም ሲል በዚሁ ፕላትፎርም ላይ ያሠፈረውን መልዕክት ጠቅሼ ወደ መጠሁበት ጉዳይ መግባት ፈለግሁ። ወንድማችን የቀድሞ አሥመራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ሕይወት እንዲህ ሲል ገልፆታል፥
የኢሠፓ ሚስት ድንገተኛ ፍቅርና ጭንቀት
የማያልቅ የለምና የዩኒቨርሲቲ ት/ት አልቆ ተመርቀን በዕጣ የሀገር ዉስጥ ንግድ ሚ/ር ደርሶኝ ወደ አዲስ አበባ መጣን።እናት ዩኒቨርሲቲያችን በዕዉቀት አንጻን ተመላለሰን እንደምንጠይቃት ቃል አስገብታን በእምባ ሸኘችን።
አሰመራ ቤተመንግስት ገብቼ ሊተኮስብኝ ነበር
1978 መሆኑ ነዉ።ገና ፍሬሽ ሆነን ከገባን ወርም የሞላን አይመስለኝም።እንዲሁ መንገድ ላይ ባጋጣሚ የተዋወኩት ከኢሉባበር የመጣ ተራ ወታደር በዛኑን ማታ ቤተመንግሥት ጠባቂ ስለሆነኩ ጎራ በል አለኝ።እራቴን በልቼ በጥቆማዉ መሠረት ሄድኩ።
የ50 ሳንቲም ዶሮ የብር ገመድ ይዛ ጠፋች
እስክርብቶ አልቆብኝ ነገ ምን ይዤ ክፍል እገባለሁ እያልኩ ከላሳሌ ለራት ወደ ዋና ግቢ ብቻዬን ጉዞ ጀመርኩ።አንድ ዘናጭ ጫማ ብቻ ናት የነበረችኝ።አንድ ሌላ አሮጌ ለኔ ብጤ ጓደኛዬ ሰጥቼ ነበር።እሱ ደግሞ ጫማ አልቆበት በስሊፐር መሄድ ጀምሯል።
የጎሬዋ ያንድ ቀን ፍቅር
ጎሬ ባትሄዱም ላንድ ቀን የኢትዮጽያ ዋና ከተማ እንደነበረች ወይ ተምረናል ወይ ሰምተናል።አይቻታለሁ።ተራራ ላይ የቆመች ከተማ ናት።ከመቱ 25ኪሜ ትርቃለች።መቱ ከበደሌ 120ኪ ሜ ትርቃለች።በደሌ ከአዲስ አበባ 480 ኪሜ ናት።ጊዜዉ 1978 ዩኒቨርሲቲ መግቢያችን ነበር።ያለፍኩት በጅማ በኩል በደሌ 60 ኪ ሜ ሲቀር ደምቢ ከሚትባል ከተማ ነበር።
የዘመኑ ሳይንቲስትና ምርጥ ሰው (ዶ/ር ተወልደ)
ዶ/ር ተወልደ ያረፉት መጋቢት 12/2015 ነው፡፡ ዛሬ 2ኛ ሙት ዓመታቸው ነው፡፡ ስለዚህ ስለሳቸው ከተጻፉት ውስጥ ለየት ያሉትን፣ ብዙም ያልተወሱትንና በግለ-ታሪካቸው ያልተዳሰሱ አንዳንድ ነጥቦችን እያነሳን ሰሞኑን እንዘክራቸዋለን!
ዶ/ር ጌታቸው ቦሎድያ በአስመራ
ሙሴ (መሴ-ቬኖ) አብዛናውን ነገር በትክክል ገልጸኸዋል። ፕሮፌሰር እንደሻው (የያን ጊዜው ዶ/ር) የሳይንስ ፋኩልቲ ዲን ስለነበሩ የልምድ ልውውጥንና የዕውቀት መጋራትን ከማጎልበት አኳያ ይመስላል አንጋፋ ምሁራንን ይጋብዙ ነበር። ከዶ/ር ጌታቸው በተጨማሪ ፕሮፌሰር ሳምነር የተባሉ (አውሮፓዊ ይመስሉኛል) የፍልስፍና ሰውን መጋበዛቸው ትዝ ይለኛል። ዶ/ር ጌታቸው ሌክቸር የሰጡት በኦዲቶሪዬም ነበር።
የካምፓሱ አመፅና ውጤቱ..
ላሳሌን በኔቪ ተቀምተን ከአብዮት አደባባዩ ሁዋላ ማይ ጩኸት የሚባል ሰፈር ኔቪ የለቀቀው ካምፕ በመግባታችንና በጣም እሩቅ ስለነበር አንማርም ብለን ስለነበር ጉዋድ ካሳዬ አራጋው የመጡት:: ብዙ ቢያስፈራሩንም በፍጥነት ቻው ሆቴል እና ገማግል አስገቡን:: ቅርብ ቦታ- ከላሳሌም የቀረበ::
ስንቱ ስንቱ......ይታወስ
የካራቭል እና ፍራፍሬ (ኮምፒሽታቶ ያለው ) ጁስ ቤት ባናና ጁስ በአንድ ብር : ምርጥ ኬክ በሀያ አምስት ሳንቲም: ንፁህ ቡና ማኪያቶና ካፑቺኖ በሀያ አምስት ሳንቲም: ከላሳሌ በር ፊትለፊት ባለው መንገድ አንድ ብሎክ ሄደን ያለች ካፌ በርገር በአንድ ብር: ኮምፒሽታቶ እርጎ በማር ሀምሳ ሳንቲም?:
እባክህ ቀንስልኝ..
አስመራ እቃ ተከራክሮ ዋጋ ማስቀነስ አይቻልም ነበር።ሬድዮ ማዳመጥ እወድ ስለነበር አስመራ እንደገባው ኮምፑሽታቶ ወደሚገኝ አንድ ሱቅ ጎራ በዬ አነስተኛ ሬድዮ ጠይቄ ባለሱቁ አንዲት ቀይ የምታምር ትንሽዬ PHILIPIS ሬድዮ አሳየኝናዋጋ ነገረኝ ።እኔም እዚህ መሃል አገር እንደለመድነው መስሎኝ ቀንስ አልኩት
አሞይ አምለሰትና የካራቬሉ አስተናጋጅ
የአሥመራ እናቶች "እናትነት" ተዘክሮ የሚያልቅ አይደለም። በብዙዎቻችሁ የሚሰጠው ምስክርነት ሳነብብ እኔ ለመጻፍና ለመግለጽ የሞከርኩት 'ኢምንት' ይሆንብኛል።
መጽሐፍ መደበቅስ?
አቤ ስለ ላይብረሪ ስታነሺ ጓደኛዬ የነገረኝ ትዝ አለኝ። ለቋንቋ ተማሪዎችአንድ ከባድ የfiction መጽሐፍ እንዲገመግሙ የቤት ሥራ ተሰጣቸዉ።
አለሙ አሰፋ ሙሉነህ
ዓለሙና እኔ የአዲስ አበባ ልጆች ነን፤ እሱ ጉለሌ (መድኃኒያለም ት/ቤት ነው የጨረሰው)፣ እኔ ሊሴ ገ/ማርያም ወይም ቴዎድሮስ አደባባይ ጥቁር አንበሳ ት/ቤት፡፡
ቀኛዝማች መብራቱ
አዎ ቀኛዝማች በጣም አስቂኝ ነበሩ "አንድ secretarial science ተማሪ በብሄራዊ ውትድርና ልዩ ድጋፍ የገባ ተማሪ የነገረኝን ላጫውታችሁ ልጁ መጀመርያ ሲመደብ Management degree ተመደብኩ
ሀብቴና እስማኤል..
ይሄ የዋትስ አፕ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ብዙዎቻችንን ብቻ ሳይሆን ሁላችንንም እርስ በእርስ እንድንገናኝ አስተዋጽኦው ብዙ ነው። እኔ እራሴ ብዙዎች ጋር ተገናኝቻለሁ፣
ያልተሸጠው ከስክስ ጫማ
ሁለተኛ አመት (1975ዓም) እያለን ትዛዙ ዘነበ ( ጂሌቲ) የሚባል ጓደኛችን ጦር መስመር ያለው መቶ አለቃ የሆነ ወንድሙ የወታደር ጫማ ከስክስ ላከለትና የናዝሬት ልጆች የሆንን አንድ አምስት ጫማውን ልንሸጥና