አሰመራ ቤተመንግስት ገብቼ ሊተኮስብኝ ነበር

1978 መሆኑ ነዉ።ገና ፍሬሽ ሆነን ከገባን ወርም የሞላን አይመስለኝም።እንዲሁ መንገድ ላይ ባጋጣሚ የተዋወኩት ከኢሉባበር የመጣ ተራ ወታደር በዛኑን  ማታ ቤተመንግሥት ጠባቂ ስለሆነኩ ጎራ በል አለኝ።እራቴን በልቼ በጥቆማዉ መሠረት ሄድኩ።

ከhigh school ክረምት ስመለሰ በገጠር ከተማና ገጠር እንደመንሸራሽር ቀላል መስሎኝ ነዉ።ቶክስና አስፈሪዉን  ወታደራዊ ትዕዛዝም ሰምቼ አላውቅም።ከሚሽቱ 1:30 ይሆናል።ጨለምለም ብሏል።ከሁለት ወገን የሚጠብቁትን ወታደሮች ሳላይ እጄን ኪሴ ዉስጥ ከትቼ ወደ ዋና በር ጉዞዬን ቀጠልኩ።አዉቆ ወደላይ አሳለፉኝ መሰለኝ ለመጀመሪያ በር ተቃርቤአለሁ።ባንዴ ከሀለቱም አቅጣጫ  የቁም ቁም ዉርጅብኝ ለቀቁብኝ።ሰለማላውቅ መደንገጥ የነበረብኝን ያህል አልደነገጥኩም።ግን እጄን ከኪስ አዉጥቼ ቆምኩ።በአራት አቅጣጫ መጡብኝ።ማነህ ምንድነህ  አሉኝ።የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነኝ አንድ የክ/ሀገሬ ልጅ በዚህን ሰዓት ቀጥሮኝ መጣሁ አልኳቸዉ።ማነዉ አሉኝ።ስሙን ነገርኳቸዉ።እንዲህ የሚባል እዚህ የለም አሉኝ።ፍርሃቴ አሁን ገና ጨመረ።የት እንደመጣህ ታዉቃለህ አለኝ።ቤተመንግሥት አልኩት።አላዋቂ መሆኔን ተረዱ።እርጋታቸዉ ይደነቃል።አስመራን ታዉቃለህ አሉኝ።ገና አላወኩም አልኩ።ባይነግሩኝም ሳያዝኑልኝ አልቀረም። ተረጋገተህ ወደ መኖሪያህ ሂድ አሉኝ።ወደፊት መጠንቀቅ እንዳለብኝም መከሩኝ። ባልሳሳት በወቅቱ በቤተመንግሥት  የነበሩት መሪድ ነጉሴ መሰሉኝ።ከዚያ በኋላ የቀጠረኝን ወታደር ለማግኘትም አለልፈለኩም።ሳንገናኝም ነዉ የተመረኩት።አንድ ጓደኛዬ አንድ ዓይኑ የተንሽዋረረ ነዉ። ከብዙዎች ጋር  ለቅሶ ይሄዳል።የለቅሶ ቤቱ  በር ዝቅ ያለ ነበርና ሁሉም አናተታቸዉን እየተመቱ ሲገቡ እሱ ነጻ አለፈ።ሁሉም ተመተዉ እኔ ሳልመታ አለፍኩ ብሎ ፎከረ ።አንድ ሊያበሽቀዉ የፈለገ  ጓደኛዉ ህጻንንና ዓይነ ሰዉርን ፈጣሪ ይጠብቃቸዋል አለዉ።እኔንም ባላገርነቴን አይቶ  ፈጣሪ ተፋኝ ለማለት ይቻላል።ኢሉባቦርም ስላልኩ ከሰሜኑ ጦርነት ቦታ ከ1500ኪሜ ከሚርቅ ቦታ መምጣቴንም  ከግምት አስገቡ መሰለኝ መክረዉ ለቀቁኝ።እዚያ እያለሁ እንዳይሳቅብኝ ብዬ ለማንም አልተነፈስኩም።ከተመረኩ ወዲህ፣አስቂኝ መስሎ ስላልታዬኝ ለማንም አልተናገርኩም።ይሄዉ ሳንወድ ፍርድ እንዲሰጠን  ለማህበራችን  መናዘዝ ጀምረናል።

Previous
Previous

የኢሠፓ ሚስት ድንገተኛ ፍቅርና ጭንቀት

Next
Next

የ50 ሳንቲም ዶሮ የብር ገመድ ይዛ ጠፋች