ስንቱ ስንቱ......ይታወስ
1. የካራቭል እና ፍራፍሬ (ኮምፒሽታቶ ያለው ) ጁስ ቤት ባናና ጁስ በአንድ ብር : ምርጥ ኬክ በሀያ አምስት ሳንቲም: ንፁህ ቡና ማኪያቶና ካፑቺኖ በሀያ አምስት ሳንቲም: ከላሳሌ በር ፊትለፊት ባለው መንገድ አንድ ብሎክ ሄደን ያለች ካፌ በርገር በአንድ ብር: ኮምፒሽታቶ እርጎ በማር ሀምሳ ሳንቲም?:
2. አስመራማ ይለያል አንዴ ከፍለን እየደጋገምን የምናይባቸው ፊልም ቤቶች
3. የሚገርመኝ ሌላ ነገር መሀል አገር ዋጋ የሌላት አንድ ሳንቲም ዋጋ ያላት አስመራ ብቻ ነበር:: የአንድ ሳንቲም መልስ ሁሉም ይቀበላል:: አልፎ አልፎ በልመና ላይ የተሰማሩ የኔብጤዎች ፊት የተከመሩ አንድ ሳንቲሞች ማየት የተለመደ ነበር::
4. ከየትኛውም ቦታ ይልቅ በክብር የሚታይ እስፖርት ብስክሌት ውድድር ነበር: በየመንገዱ ስቴጅ ተሰርቶ ከአዋቂ እስከ ልጅ ወንዱም ሴቱም ውጥቶ የሚያየው:
5. የአስመራ ሽክ ያሉ ሹራቦች ሲወደዱ 50 ብር : ዘናጭ የጣልያን የሚመስሉ ጫማዎች ከ30 - 50 ብር ተዘነጠበት:
6. የምድረ ገነት ክትፎ: ማነው ስሙ (ሹቅ ያለው የጎንደሬው ሰውዬ) ጥብስ ቤት: ፎርማጆና ሞርቶዴላ:
7. ሜይን ካምፓስ ግቢ ውስጥ የነበረው የአደይ ለምለም ሻይ ቤት ውስጥ ይሸጥ የነበረው ሰላጣ በድንች ቅቅል
8. ዋናው ካምፓስ ፊት ለፊት ዳቦ የምንሸጥበት የነበእምነት ሱቅ:
9. ማይ ጋዝ በጠርሙስና በቢኬሪ ስንት ስንት ነበር?
ስንቱ ስንቱ......ይታወስ