እባክህ ቀንስልኝ..

አስመራ እቃ ተከራክሮ ዋጋ ማስቀነስ አይቻልም ነበር።ሬድዮ ማዳመጥ እወድ ስለነበር አስመራ እንደገባው ኮምፑሽታቶ ወደሚገኝ አንድ ሱቅ ጎራ በዬ አነስተኛ ሬድዮ ጠይቄ ባለሱቁ አንዲት ቀይ የምታምር ትንሽዬ PHILIPIS ሬድዮ አሳየኝናዋጋ ነገረኝ ።እኔም እዚህ መሃል አገር እንደለመድነው መስሎኝ ቀንስ አልኩት ዋጋው ነው አለኝ ተማሪ ነኝ እባክህቀንስልኝ አልኩት አሁንም ያንኑ ደገመልኝ ለሶስተኛ ጊዜ ስጠይቀውተናዶብኝ ወንድሜ አዲሳባ ሂድና ተከራክረህ ግዛብሎ ቆሌዬን ገፎኝ ሬድዮውን ተቀበለኝ እኔም እንደማያዋጣኝ ተረድቼ መጀመሪያ የነገረኝን 26 ብር ከፍዬ  ትንሽየዋንሬድዮዬን ይዤ ወደ ላሳሌ አመራሁ

Previous
Previous

ስንቱ ስንቱ......ይታወስ

Next
Next

አሞይ አምለሰትና የካራቬሉ አስተናጋጅ