ቢያቲ ቢያቲ!

እኔ የመጨረሻ Batch ነኝ 1989/90(1982)እና ከደብረዘይት አየር ሃይል በራሺያ አውሮፕላን አስመራ 5 ሰአት ላይ ገባን በኮስተር(የዩኒቨርስቲው) መኪና "ማይ ጩሖት" የሚባል አዲስ የባህር ሃይል የነበረ ካምፓስ ገባን ቀጥሎ አንድ ሌሊት ያደርንበት Dormitory ተሰጠን አንድ በዚያው ቀን የተዋወቅኩት ጉዋደኛየ ጋር ወደ ዋናው ጊቢ main campus "እምባጋልያኖ" ለምሳ ከብዙ ዙረት በሁዋላ ደረስን። ወደ ካፌ ተሰልፈን ስንገባ በቅፅል ስሙ "ማሞ" የሚባል ወጥ የሚጨልፍ ልክ ስሓን ልናነሳ ስንል ስሃን አለቀ ፥እኔ ከፊት ነበርኩና ከቤተስቦቼ የለመድኩት እና ትግርኛ እሰማለሁ እና ጎላውን በጭልፋ እየደበደበ "ቢያቲ !ቢያቲ !' ሲል በጣም ቀጭን ሴትዮ የታጠበ ሰሃን ደርድረው ይዘው መጡ እኔም አነሳሁ ሶስት" ባኒ"(ዳቦ ) ተደረገልኝ እና ወጥ ሲጨለፍልኝ ከሁዋላየ ያለው ጉዋደኛየ ሰሃን ሲያነሳ የዳቦ ቁራጭ አገኘ እና የታጠበ ሰሃን ያመጡልን ቀጭን አሮጊት ሴትዩ ጋ ዘወር ብሎ "አደይ ቢያቲ" ይህን ሰሃን ቀይሩልኝ ሲል ..።ሴትዮዋ በጩኸትና በቁጣ መሳደብ ጀመሩ ጉዋደኛየ ደነገጠ እኔና "ማሞ" ጬላፊው እንስቃለን ሴትዮዋ በትግርኛ ይሰድቡታል እኔም እየሳቅኩ ምሳ ከበላን በሁዋላ ለምን "አደይ ቢያቲ" አልካቸው ስለው ወደካፌ ስንገባ "ቢያቲ !ቢያቲ!" ሲል ጨላፊው ማሞ ሴትዮዋ ሰሃን ይዘው ሲመጡ ስማቸው ቢያቲ መሰለኝ አለኝ "ቢያቲ" ማለት ግን በጣልያን እና በትግርኛ ሰሃን ማለት ነው

Previous
Previous

አለሙ አሰፋ ሙሉነህ

Next
Next

ቀኛዝማች መብራቱ