ቀኛዝማች መብራቱ
አዎ ቀኛዝማች በጣም አስቂኝ ነበሩ "አንድ secretarial science ተማሪ በብሄራዊ ውትድርና ልዩ ድጋፍ የገባ ተማሪ የነገረኝን ላጫውታችሁ ልጁ መጀመርያ ሲመደብ Management degree ተመደብኩ አለ አንድ ሴሚስተር ተምሬ በጣም ከበደኝና በሁለተኛው ሴሚስቴር Accounting Degree program ቀይሩኝ ብየ ቀኝ አዝማች መብራህቱ ጋር ሄድኩ second semester አካውንቲንግ ዲግሪ ቀየሩኝ፥ ስገባ የባሰ ከበደኝ እና የሚቀጥለው አመት Accounting Diploma ቀይሩኝ የድሃ ልጅ ነኝ ቶሎ ጨርሼ ቤተሰቤን ልርዳ ብየ ሳመለክት ቀኛዝማች መብራህቱ አንተ አምና ሁለት ጊዜ ቀይሬህ በል እሺ ብለው Accounting Diploma ቀየሩኝ mid semester ላይ ግን በጣም ከበደኝ እና በህክምና ማስረጃ ሳልፈተን ቀረሁና ፡ቀኛዝማች እኔ አልቻልኩም ወደ Secretariat science ቀይሩኝ ብየ ስሄድ ዋእ!ዋእ ቀስ ብለህ ደግሞ "ባርካ ወይ ቀይ ባህር "High school ቀይረኝ እንዳትለኝ እሱን አልችልም አሉኝ ያለኝ ትዝ ይለኛል በሁዋላ በ secretarial science ተመርቆ አርባምንጭ ዩኒቨርሰቲ በእጣ እንደተመደበ አውቃለሁ የት እንዳለ አሁን አላውቅም