የጎሬዋ ያንድ ቀን ፍቅር
ጎሬ ባትሄዱም ላንድ ቀን የኢትዮጽያ ዋና ከተማ እንደነበረች ወይ ተምረናል ወይ ሰምተናል።አይቻታለሁ።ተራራ ላይ የቆመች ከተማ ናት።ከመቱ 25ኪሜ ትርቃለች።መቱ ከበደሌ 120ኪ ሜ ትርቃለች።በደሌ ከአዲስ አበባ 480 ኪሜ ናት።ጊዜዉ 1978 ዩኒቨርሲቲ መግቢያችን ነበር።ያለፍኩት በጅማ በኩል በደሌ 60 ኪ ሜ ሲቀር ደምቢ ከሚትባል ከተማ ነበር።ማትሪክ ያለፈዉ ተማሪያችሁ ቡኖ በደሌ አዉራጃ ት/ጽ/ቤት መጥቶ ደብዳቤ ወስዶ የኒቨርሲቲ ይግባ ተብሎ ትዕዛዝ ተላለፈ። ነፍሷን ይማርና የጓደኛዬ የትሩፋት ከተማናት።መቱ የሟች ዳዊት ከተማ ናት።ነፍሱን ይማር።ሂደና ወስድ ተብሎ ተነገረኝ። ጂማ አድሮ የሚያልፍ አዉቶቡስ ተጠብቆ ነዉ የሚከደዉ። አዉቶቡስ ተራ ስደርስ የማዉቃቸዉ ወጣት ባልና ሚስት አስተማሪዎች ከማላዉቃቸዉ ሁለት ወጣት ሴቶች ጋር ወደ በደሌ ሊጓዙ ተዘጋጅተዋል።ተሳፍርን እንኳን ፈተና አለፍክ ከሚል ምርቃት በመጀመር ከነዚያ ጉብሎች ጋር አስተዋወቁኝ።ትልቋ አስተማሪ ናት።ትነሿ ከ18 ዓመት ዕድሜ አታልፍም።ቀኑ ሰኞ ነበር።ትልቋ የሚቀጥለዉ ሐሙስ ሊታገባ ጅማ መጥታ ለሠርጓ የሚያስፈልጋትን ገዝታ እየተመለሰች ነዉ።ባጋጣም እኔና እሷ አንድ ወንበር ላይ ተቀመጥን።ቆንጆ አልነበረችም።የደስደሷ አይጣል ነዉ።የዛኔ አዉቶቡስ በዚያ ጭቃና በተበላሸ መንገድ 30 ኪሎ ሜትር መሄዱንም እንጃ።ምን እንዳወራን ባላስታዉስም ስለሠርጉና የኔ ፈተና ማለፍን እያወገን መሰለኝ በደስታ በደሌ የደረስን።ሶስት አልጋ ያዝንና እራት በልተን እዚያዉ ሆቴል መዛናናት ጀመርን። ትንሿ ልጅ ነገራችንም አላማራትም አራት ሰዓት አከባቢ በኩርፊያ መሰል ሄዳ ተኛች።ሁለታችንም ተፈላልገናል።ጥንዶቹም ተመኝተዉልናል።እሷን እጅግ ከበዳት።ሀሙስ ልታገባ ነዉ።እነዚህ ዘመዶችዋንም አፈረች።እህቷንም ፈራች።እየተጨዋወትን ሰዓቱን ገፋን።ምናልባት አሰከ 8 ሰዓት።ከቆይታ ብዛት እነሱም ጣልቃ ገብተዉ መጠጡም እገዛ አድርጎ ተያየዘን የኔ ክፍል ገባን።ጥንዶቹ በደሌ ላይ ነዉ የሚቀሩት። እሰከ ጎሬ ከእህቷ ጋር የሚትሄድ እሷ ናት።ሀሳባችን እኔ ጋ ቆይታ ወደ በርጓ ሊትመለስ ነበር።አዉቶቡሱ የሚወጣዉ በማለዳ ነበር።ሻንጣዋ አዉቶቡሱ ለይ ነዉ ያደረዉ።ያኔ ደግሞ ኃይማኖታዊ አጢአቶች አይፈሩም። ክፍል ገብተን ተዋደድን ወደ ንጋት እንቅልፍ ወሰደን።ወደ ራሷ ከፍል አልሄደችም።ተንኮለኛ እህቷ ሳትቀሰቅሳት ማለዳ የሚወጣዉን ባስ ብቻዋን ተሳፍራ ነጎደች።ከጫቁላ ቤት ከሚመስለዉ እንቅልፍ ስንነቃ ወደ አራት ሰዓት ሆኗል።መዋደድ ሳይሆን ተሳከርን።በቃ አንተን ትቼ አልሄድም አለች።እኔ ደግሞ ትምህርቱም ገደል ይገባ ካንቺ ጋር ካልሄድኩ አልኩኝ።የሄደች የመሰለዉ አስተማሪም አይቶን ደነገጠ።ለቅሶ በለቅሶ ሆንን።በቃ ወደ 5:30 በሚደርስ አዉቶቡስ ተሳፈሪ አሏት።አልሄድም አለች።እኔ በቀደም ካልፎርኒያ ቤት እንደተቃጠለባቸዉ ሰዎች ፈዘዝኩ። ምን እንደማደርግ ገራ ገባኝ።ሌላም ሰዉ ተጨምሮ ተለመነችና በቃ እሽ አለች።እስኪዚያ ግን በይፋ የማልቀስ ነጻነታችንን አስከበርን።ባሱ መጣ።ተለምናም ተገፍታም የባሱ በሩ ላይ ስትደርስ አንደነብር ዘላ ተጠምጥማብኝ። ለቅሶ ወደ ሁለታችን ጩሄት ተለወጠ።ሰዉ ተሰበሰበ።ዉሰጥ ያሉትም ወረዱ።ማን ይለያየን።ምን ትብሎስ ይነገር?ደግሞ ቦታ የተገኘላት ባስ ዕቃዎችዋን ይዞባት ሄዶ ነዉ ተብሎ ነዉ።እያዘኑም እየተናደዱም አላቀዉን ሸኙዋት።ቀኑን መሉ እያነባሁ ዋልኩ።በዚያን ሰሞን በጣም ተከፋሁ።ከዚያ ወዲህ አላገኘሁአትም።ልቤ ግን አልፎ አልፍ የጎሬዋን ያስታዉሳታል።ፍቅር ምስጢር ነዉ።ከባድ ነዉ።