መጽሐፍ መደበቅስ?
ስለ ላይብረሪ ስታነሺ ጓደኛዬ የነገረኝ ትዝ አለኝ። ለቋንቋ ተማሪዎችአንድ ከባድ የfiction መጽሐፍ እንዲገመግሙ የቤት ሥራ ተሰጣቸዉ። አሱና ጓደኛዉ መጽሐፉን ለመረዳት አልቻሉምና አጋዥ መጽሐፍ ፍለጋ ላይብረሪ ይገባሉ።መጽሐፍ ሲፈልጉ የተገምጋሚዉን መጽሐፍ የአማርኛ ትርጉም ከላይብረሪ ውስጥ አገኙና ጮቤ ረገጡ። አራት ቅጂዎች ብቻ ነበሩ።ካሉት ቅጂዎች ሁለቱን ወሰዱና የተቀሩትን ሌሎች ተማሪዎች በማያዩአቸዉ ሥፍራ ወሽቀዉ የቤትሥራዉ እንዳለቀ በመቁጠር ዶርም ገብተዉ አማርኛዉን ማንበብ ጀመሩ።ሲያዩት በአንድ ኢትዮጽያዊ ሎሬት የተተረጎመ ሆኖ ከእንግልዝኛዉ በላይ ከብዶ አገኙት ።የቤት ሥራዉ የከበደዉ ለሁሉም ነበር።እነዚህ ተንኮለኞች የተዋሱትን 2ቱ የአማርኛ መጽሐፎችን በጧቱ ለላይብረሪ በመመለስ የደበቁትነም ጭምር ወደ ቦታዉ እንዲመለስ አደረጉ።በዚህ አላበቂም። እንደወጡ ለሌሎች ለምን አማርኛ ቅጂ አታነቡም በማለት ለሩጫና ሸሚያ ዳረጉአቸዉ።
እንዲህ አይነቱ ድራማ ትናንትም ዛሬም የደሰታ ምንጭ ነዉ።በገጠመኞቻችን ቤታችንን እናማሙቅ።