ዶ/ር ጌታቸው ቦሎድያ በአስመራ

ፈለቀ ወልደየስ

 ሙሴ (መሴ-ቬኖ) አብዛናውን ነገር በትክክል ገልጸኸዋል። ፕሮፌሰር እንደሻው (የያን ጊዜው ዶ/ር) የሳይንስ ፋኩልቲ ዲን ስለነበሩ የልምድ ልውውጥንና የዕውቀት መጋራትን ከማጎልበት አኳያ ይመስላል አንጋፋ ምሁራንን ይጋብዙ ነበር። ከዶ/ር ጌታቸው በተጨማሪ ፕሮፌሰር ሳምነር የተባሉ (አውሮፓዊ ይመስሉኛል) የፍልስፍና ሰውን መጋበዛቸው ትዝ ይለኛል። ዶ/ር ጌታቸው ሌክቸር የሰጡት በኦዲቶሪዬም ነበር። ዶ/ር ጌታቸው የዶር ተወልደ መምህር፤ ዶ/ር ተወልደ ደግሞ የፕ/ር እነደሻው (እና በኃላ ያወቅኳቸው በርካታ የአዲስ አበባ ዩኑቨርሲቲ ፕሮፌሰሮች መምህር/አባት)፤ ፕ/ር እንደሻው ደግሞ የኛ መምህር (ጀነቲክስ እና ኢቮሉሽን አስተመረውኛል) ሰለነበሩ እኛን "You are great-grand sons of Prof. Getachew" ሲሉ ነበር የገለጹት። ዶ/ር ዮሀንስ ደግሞ እጅግ የምንወደውና የምናደነቀው የ Microbiology መምህራችነ ነበር።

ስለዶ/ር ጌታቸው አስመራ ምመጣት ሳስብ አንድ ነገር ትዝ ይለኛል። ገና ዩኒበርሲቲ ሳልገባ፤ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆኜ፤ እንደዘመኑ ወጣት የራዲዮ ፕሮግራም ማዳመጥ እወድ ነበር። የእሁድ ጠዋት ፕሮግራም ደግሞእጅግ ምርጡ ነበር። ይመስለኛል ታደሰ ሙሉነህ የተባለው አንጋፋ ጋዜጠኛ ከዶ/ር ጌታቸው ጋር ቆይታ ነበረው። ዶ/ር ጌታቸውም ብዙ ፈገግ የሚያስብሉ ነገሮችን ሲያነሱ ቆይተው ስለተማሪዎቻቸው ማውሳት ጀመሩ። እንዲህም አሉ "ከተማሪዎቼ መካከል ተወለድብርሃን የሚባል አለ፤ አሁን እዚህ ቦታ ላይ በኃላፊነት ይሰራል። ታዲያ ክፍል ውስጥ ሳስተምር ልጆቹ እንደገባቸውና እንዳልገባቸው ለማረጋገጥ ተማሪዎቼን እመከታለሁ። ተወልደ ራሱን ከነቀነቀ በቅቶኛል፤ እቀጥላለሁ"። እንዲህ የተባለላቸውን ሰው ነበር ከጥቂት ጊዜ በኋላ ፕሬዚዳንቴም አስተማሪየየም ሆነው ያገኘኋቸው (ከ General Ecology ኮርስ አንድ ቻፕተር ስላስተማሩን)። ለመሆኑ ለመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መሰረት መጣል ቀዳሚው ሚና የነበራቸው ዶ/ር ተወልደ መሆናቸውን ስንቶቻችን እናውቃለን። እኔም ስለጉዳዩ በቅርቡ ነው ያወቅኩት፤ አብሯቸው ከሠራ የቅርብ ወዳጄ። ወደፊት ስለዶ/ር ተወልደ ለፎረሙ የምናጋራው አንድ ሃሳብ አለ። በግሮቭ ጋርዱኑ መድረክ ከተገኘችው ልጃቸው ጋር በጥቂቱ አውርተናል። አርአያዎችችንን ማክበርና ማስከበር መልካም ምግባር ይመስለኛል።

ዶር አበበ አምሀ

ዶ/ር ጌታቸው ቦሎዲያን በቅርብ የሚያውቅ አንድ ታላቅ ሰው ያጫወተኝ ነገር፦

መነሻው እዚያው አራት ኪሎ ግቢ ስታፍ ሆኜ ጥበቃዎቹን በደንብ ሠላም ስል አይቶ ያስታወሰውን ነገር ነገረኝ። 

" ጌታቸው ሽቁጥቁጥ ብሎ ኮፍያም ካደረገ አውልቆ አንገቱን ዝቅ አድርጎ ሠላም የሚለው ዘበኞችን ብቻ ነው፤ ለሌላ ሰው ደንታ የለውም። ምክንያቱ ደግሞ ዘበኛ ከጠመመብህና አትገባም ካለህ የትም ምንም ማድረግ አትችልም። ከገባህ በኋላ ግን ባለሥልጣን ይሁን ምሁር የፈለግከውን መናገርና ማድረግ ትችላለህ። ቢሮህ እንኳ መግባትና መሥራት ትችላለህ የሚል ነበር። ልክ ነበር። እኔም ይህንን አቀራረብ እጠቀምበታለሁ።

 

ሰለሞን

አንዴ ጓድ መንጌ ቤተመንግስት ይጠራዋል ለጉዳይ። ዶር ጌታቸው ቦሎዲያ አንሶላ፣ብርድልብስ ምናምን ይዞ ይሄዳል፡ታዲያ መንጌ ገርሞት ምንድርን ነው ይሄ ሁሉ ኮተት ዶር ጌታቸው ሲለው፣ምን ይታወቃል የርሶ ነገር ካሰሩኝም በዚሁ ልግባ ብዬ ነው አለ ይባላል።

ምንጭ ስለሱ ዝም ብለው ከሚወሩ ነገሮች የሰማሁትን።

ታዜ

ኢትዮጵያ ብዙ ብርቅየ ሙህራንን አጥታለች። ዶ/ር ጌታቸው እውቅ ሙህር ብቻ ሳይሆን ለአመነበትም ደፋር ነው ይባላል። የማይወደው ያለ ስራ ቆሞ መቆየትን ነው; ለዚህ መግለጫው የትራፊክ መብራት ጥሶ ይሄዳል ይባላል። ታዲያ አንድ ቀን ቀይ መብራት ጥሶ ሲሄድ ትራፊክ ይዞ ይጠይቀዋል; እኔ አስቸኳይና ብዙ አጣዳፊ ስራ አለብኝ ቶሎ ደርሸ እንዳልሰራ የምታደርጉኝ ይህ መብራትና እናተ የቆማችሁ ሰወች ናችሁ; ለማንኛው ጓድ መንግስቱ ቶሎ ድረስ ስላሉኝ ነው የምትለውን በልና ልሂድበት እንዳታስቀጣኝ ሲለው ሞቅ ያለ ሰላምታ ሰጥቶ ለቀቀው ይባላል። እውነት ይሁን አባባል እኔ ሀላፊነቱን አልወስድም። አንዳንዴ የማይጎዳ ጥበብ ያለው ማምለጫ ውሸትም ይጠቅማል ማለት ነወ?

Previous
Previous

የሰሌ ስናኮች

Next
Next

የካምፓሱ አመፅና ውጤቱ..